የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life! የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ On Oct 8, 2026 አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ስትራቴጂያዊ አጋርነት ከፍተኛ ክብር እንደምትሰጥ አውስተው፤ የሁለቱን ሀገራት ትብብርና ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕንድ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊነት ውስጥ ለ25 ዓመታት በማገልገል የብር ኢዮቤልዩ በዓላቸውን እያከበሩ ለሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በትናንትናው ዕለት የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አመስግነው፤ ቀጣይ የኃላፊነት ጊዜያቸው ስኬታማ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like የሀገር ውስጥ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት አስተላለፉ የሀገር ውስጥ ዜና ከአፍሪካ አንድነት ርዕይ ጋር የተሳሰረው የኢትዮጵያና ናይጄሪያ ግንኙነት የሀገር ውስጥ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ የሀገር ውስጥ ዜና ከመብሰልሰል ወደ መወሰን – ኢትዮጵያን ወደ ቦታዋ More Stories ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት… Oct 7, 2026 ከአፍሪካ አንድነት ርዕይ ጋር የተሳሰረው የኢትዮጵያና ናይጄሪያ ግንኙነት Oct 7, 2026 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ Oct 7, 2026 1 of 15,856

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button