አይ ኤም ኤፍ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ሊያጠናክር ይገባል-ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)

አይ ኤም ኤፍ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ሊያጠናክር ይገባል-ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)

አይ ኤም ኤፍ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ሊያጠናክር ይገባል-ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life! አይ ኤም ኤፍ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ሊያጠናክር ይገባል-ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) On Oct 15, 2026 አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ሊያጠናክር ይገባል አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)፡፡ የአፍሪካ ብሔራዊ ባንክ ገዥዎች ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ጋር በባንኮክ ተወያይተዋል፡፡ በመድረኩ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ÷በኢትዮጵያ የተደረገው ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ማረጋጋት መቻሉን እንዲሁም አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን እየከፈተ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ታዳጊ የአፍሪካ ሀገራት የማይበገር ኢኮኖሚ እንዲገነቡ ለማስቻል ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አጋርነቶችን እና ጥልቅ ማሻሻያዎችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የአፍሪካ ብሔራዊ ባንክ ገዥዎች በበኩላቸው ÷በመዋቅራዊ ማሻሻያዎች፣በፈጠራ እና በቀጣናዊ ውህደት አማካኝነት የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ አቅም ወደ ዘላቂ ዕድገት ለመለወጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ የአፍሪካ የባንክ ገዥዎች ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የአፍሪካ ታላላቅ የልማት ፕሮጄቶችን በፋይናንስ እንዲደግፉ ጥሪ ማቅረባቸውን የብሔራዊ ባንክ መረጃ አመላክቷል፡፡ FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like የሀገር ውስጥ ዜና ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ነገ ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል የሀገር ውስጥ ዜና የመንግሥት ቁርጠኝነት ለትግራይ ሕዝብ ሰላም የሀገር ውስጥ ዜና ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች የሀገር ውስጥ ዜና ኢትዮጵያዊ ስልጣኔ መገንባት – ኑ የኢትዮጵያን ስልጣኔ አብረን እንገንባ More Stories ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ነገ ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል Oct 16, 2026 የመንግሥት ቁርጠኝነት ለትግራይ ሕዝብ ሰላም Oct 16, 2026 ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና… Oct 16, 2026 1 of 15,911

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button