የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ለኤርትራ ሕዝብ ስጋት ሆኖ አያውቅም – የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ለኤርትራ ሕዝብ ስጋት ሆኖ አያውቅም – የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ለኤርትራ ሕዝብ ስጋት ሆኖ አያውቅም – የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life! የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ለኤርትራ ሕዝብ ስጋት ሆኖ አያውቅም – የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል On Oct 15, 2026 አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የኤርትራ ሕዝብ ስጋት ሆኖ አያውቅም አለ የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል። የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል የዲፕሎማሲ ኃላፊ ዮኤል ዮሀንስ ፥ ለ35 ዓመታት ኤርትራን የግል እስር ቤት ያደረገው የኢሳያስ አፈወርቂ ሥርዓት የኢትዮጵያን የአብሮ መልማት ጥያቄ ጥላሸት ለመቀባት የሚሄድበት መንገድ የኤርትራ ሕዝብ አቋም እንዳልሆነ አንስተዋል። የኤርትራ ሕዝብ ልማትና ፍትሕ የናፈቀው በመሆኑ ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመልማት ፍላጎት ያለው ቢሆንም በአምባገነናዊው ሥርዓት ግን ይህ ፍላጎቱ ሲጨናገፍ እንደኖረ ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ ለኤርትራ ስጋት ሆና አታውቅም ያሉት አቶ ዮኤል ዮሐንስ÷ ኢትዮጵያ ያነሳችው የባሕር በር ተጠቃሚነት ጥያቄ ለኤርትራዊያን የአብሮ ማደግ እድል እንጂ እንደ ስጋት የሚታይ አይደለም ብለዋል። በአስመራ የሚገኘው የአዛውንቶች ስብስብ ግን ከካይሮ ተልዕኮ እየተቀበለ የኢትዮጵያን ፍትሃዊ ጥያቄ ለማጨናገፍ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የኤርትራዊያን የደኅንነት ዋስትና እንጂ ስጋት አለመሆኗን በመላው ዓለም የሚገኙ ኤርትራዊያን እንደሚረዱ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like የሀገር ውስጥ ዜና ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ነገ ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል የሀገር ውስጥ ዜና የመንግሥት ቁርጠኝነት ለትግራይ ሕዝብ ሰላም የሀገር ውስጥ ዜና ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች የሀገር ውስጥ ዜና ኢትዮጵያዊ ስልጣኔ መገንባት – ኑ የኢትዮጵያን ስልጣኔ አብረን እንገንባ More Stories ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ነገ ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል Oct 16, 2026 የመንግሥት ቁርጠኝነት ለትግራይ ሕዝብ ሰላም Oct 16, 2026 ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና… Oct 16, 2026 1 of 15,911

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button