የተሾሙ ሚኒስትሮች ለማህበረሰቡ የቀረበ ሥራን መሥራት መርህ ሊያደርጉ ይገባል – የምክር ቤት አባላት

የተሾሙ ሚኒስትሮች ለማህበረሰቡ የቀረበ ሥራን መሥራት መርህ ሊያደርጉ ይገባል – የምክር ቤት አባላት

የተሾሙ ሚኒስትሮች ለማህበረሰቡ የቀረበ ሥራን መሥራት መርህ ሊያደርጉ ይገባል – የምክር ቤት አባላት – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life! የተሾሙ ሚኒስትሮች ለማህበረሰቡ የቀረበ ሥራን መሥራት መርህ ሊያደርጉ ይገባል – የምክር ቤት አባላት On Oct 8, 2026 አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተሾሙ ሚኒስትሮች ለህዝብ የቀረቡ ሥራዎችን መሥራት መርህ ሊያደርጉ ይገባል አሉ የምክር ቤት አበላት። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። በዚህም በመደበኛ ስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔያቸውን እጩዎች አባላት ዝርዝር አቅርበው በምክር ቤቱ ፀድቋል። የ22ቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የቀረቡ ዕጩዎችን አስመልክቶ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት÷ የተሾሙ የምክር ቤት አባልት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የሚወጡ እና የሚመሩ ሊሆኑ እንደሚገባ አመልክተዋል። የተሾሙት የካቢኔ አባላት በልዩ ዕይታ የተመረጡ ናቸው ተብሎ የታመነባቸው እንደሆኑ አንስተው ነገር ግን በሥራ ዘመናቸው ለማህበረሰቡ የቀረበ ሥራን መሥራት መርህ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር እንደሆነች እና ባለፉት ጥቂት ዓመታትም ከብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆና ብዙ ለውጦችን እንዳስመዘገበች ገልጸው ይህን እድገቷን ለማስቀጠል ብሎም ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ማስተካከል ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል። #የመደመር_መንግሥት FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like የሀገር ውስጥ ዜና የካቢኔው ሹመት ህብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን የሚያንፀባርቅ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሀገር ውስጥ ዜና ካቢኔውን በፍትሃዊነትና አካታችነት ለማደራጀት ጊዜ ተሰጥቶ ተሰርቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሀገር ውስጥ ዜና ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የቀረቡለትን የሚኒስትሮች ሹመት አጸደቀ የሀገር ውስጥ ዜና ሹመት ብዙ ኃላፊነት እና ድካም ያለው ጉዳይ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) More Stories የካቢኔው ሹመት ህብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን የሚያንፀባርቅ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር… Oct 8, 2026 ካቢኔውን በፍትሃዊነትና አካታችነት ለማደራጀት ጊዜ ተሰጥቶ ተሰርቷል – ጠቅላይ… Oct 8, 2026 ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የቀረቡለትን የሚኒስትሮች ሹመት አጸደቀ Oct 8, 2026 1 of 15,858

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button