የሀገርን ጥቅም ለማስጠበቅ ልዩነትን በውይይት መፍታትና በትብብር መስራት ይገባል – አቶ ሙሳ አደም

የሀገርን ጥቅም ለማስጠበቅ ልዩነትን በውይይት መፍታትና በትብብር መስራት ይገባል – አቶ ሙሳ አደም

የሀገርን ጥቅም ለማስጠበቅ ልዩነትን በውይይት መፍታትና በትብብር መስራት ይገባል – አቶ ሙሳ አደም – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life! የሀገርን ጥቅም ለማስጠበቅ ልዩነትን በውይይት መፍታትና በትብብር መስራት ይገባል – አቶ ሙሳ አደም On Oct 8, 2026 አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገርን ጥቅም ለማስጠበቅ ልዩነትን በውይይት መፍታትና በትብብር መስራት ይገባል አሉ የሰላም ሚኒስትር ሙሳ አደም። የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በካሄደው 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡለትን የካቢኔ አባላት ሹመት ያጸደቀ ሲሆን÷ በዚህም አቶ ሙሳ አደም የሰላም ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ሚኒስትሩ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ሰላም የሁሉ ነገር መሠረት በመሆኑ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል። ሰላም በመንግሥትና ሕዝብ ትኩረት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፤ ሚኒስቴሩ ቁልፍ ግቦችና ስትራቴጂዎች እንዳሉት አስረድተዋል። እነዚህን ግቦች ከዳር ለማድረስና ኢትዮጵያ የምትጠይቀውን የሰላም ፍላጎትና መሻት ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አመልክተዋል። ያለችን አንድ ሀገር በመሆኗ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ በውይይት በመፍታት በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተጀመረው አካታች የፖለቲካ ልምምድ እና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር የሚከናወነው ሥራ አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት። ለሕዝባችን እና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ከሰላም ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሁኔታዎች በተቻለን አቅም በትጋት እንሰራለን ብለዋል ሚኒስትሩ። በትዕግስት ግዛቸው FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like የሀገር ውስጥ ዜና ሙስናን የመታገል ቁርጠኝነት የሀገር ውስጥ ዜና ሥልጣን ኮፍያ እንጂ… የሀገር ውስጥ ዜና የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ የሀገር ውስጥ ዜና አዲሱ ካቢኔ መደመር በተግባር – ጥንካሬን ማስቀጠል፣ አዲስ አቅም መጨመር More Stories ሙስናን የመታገል ቁርጠኝነት Oct 9, 2026 ሥልጣን ኮፍያ እንጂ… Oct 9, 2026 የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ Oct 8, 2026 1 of 15,864

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button